20ኛው የ2015 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር እየተካሄደ ነው

995

አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ) በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚዘጋጀው 20ኛው 2015 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር እየተካሄደ ነው።

ውድድሩ  መነሻና መድረሻውን አዲስ አበባ ቦሌ አትላስ አካባቢ አድርጎ እየተካሄደ ነው።


 

የዘንድሮው ዓመት ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሎ ሜትር ሩጫቦታዬ፤ መብቴ፤ ድምፄበሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው።

በዚህ ውድድር ላይ በአትሌቶች፣ የጤና ሯጮች፣ እንዲሁም አምባሳደሮች ይሳተፋበታል።


 

በውድድሩ በሴት አትሌቶች መካከል በሚደረገው ፉክክር በአንደኝነት ለምታጠናቅቀው አትሌት 70ሺህ ብር ሽልማት መዘጋጀቱም ታውቋል።

እንዲሁም ውድድርን ሁለተኛ ሆና ለምታጠናቅቅ 45ሺህ ብር 3 ሆና ለምታጠናቅቅ ደግሞ 30ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት መዘጋጀቱም ተጠቁሟል።


 

ክብረ-ወሰን የሚያሻሽሉ አትሌቶች ተጨማሪ የገንዘብ ሽልማት የሚያገኙ ይሆናል።

በውድድሩ በአትሌቶች መካከል ከሚደረገው ውድድር በተጨማሪ 15ሺህ የጤና ሯጮች እየተሳተፉ ነው።


 

በሩጫ ውድድሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ፣ አትሌት መሰረት ደፋር እና አትሌት ለተሰንበት ግደይ ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም