የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በማስመረቅ ላይ ነው 


አዲስ አበባ መጋቢት 16/2015(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በማስመረቅ ላይ ነው። 

በቢሾፍቱ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ እየተካሄደ ባለው የምርቃት ስነ-ስርአት ላይ ከፍተኛ መኮንኖች፣ የተለያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች ፣ተመራቂ ተማሪዎች ተገኝተዋል። 


 

ዩኒቨርሲቲው  ዛሬ የሚያስመርቃቸው ተማሪዎች በምህንድስናና በጤና ትምህርታቸውን በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ የተከታተሉ ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው ከተመሰረተ 25 ዓመት ሆኖታል።

ዩኒቨርሲቲው ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ውጪ ከደቡብ ሱዳን፣ ከሱዳን እና ሩዋንዳ ከመሳሰሉ  አገራት የመጡ ተማሪዎችንም አሰልጥኖ አስመርቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም