በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እየተካሄደ ባለው የአትሌቲክስ ውድድር በስሉስ ዝላይ ዶል ማችናና በፀሎት አለማየሁ አሸናፊ ሆኑ

477

አዲስ አበባ መጋቢት 15/2015(ኢዜአ) በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እየተካሄደ ባለው የአትሌቲክስ ውድድር  በስሉስ ዝላይ በወንዶች ዶል ማችና በሴቶች በፀሎት አለማየሁ አሸናፊ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ የአጭር፣ መካከለኛ፣ 3ሺህ ሜትር መሰናክል፣ እርምጃና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እየተካሄደ ሲሆን ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።


 

በዛሬው ውሎ የወንዶችና የሴቶች ስሉስ ዝላይ ፍጻሜን ጨምሮ ሌሎች የማጣሪያ ውድድሮች ተደርገዋል።

በወንዶች ስሉስ ዝላይ ከንግድ ባንክ ዶል ማችና 16 ሜትር 22 ሴንቲ ሜትር በመዝለል የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ መሆን ችሏል።

ኪትማን ኡጅሉ፤ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ 15 ሜትር 72 ሴንቲ ሜትር በመዝለል ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ማግኘት ችሏል።

አዲር ጉር ከመቻል 15 ሜትር 69 ሴንቲ ሜትር በመዝለል የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ በመሆን አጠናቋል።


 

በሴቶች ስሉስ ዝላይ ውድድር በፀሎት አለማየሁ ከመቻል 12 ሜትር 80 ሴንቲ ሜትር በመዝለል የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች።


 

እንዲሁም ፖች ኡመድ ከንግድ ባንክ 12 ሜትር 68 ሴንቲ ሜትር በመዝለል ሁለተኛ ስትወጣ ኦባንግ አዶላ ከመቻል 12 ሜትር 64 ሴንቲ ሜትር በመዝለል ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆናለች።

በዛሬው እለት ከተደረጉ የፍጻሜ ውድድሮች በተጨማሪ 1ሺህ 500 ሜትርና 400 ሜትር መሰናክል ጨምሮ ሌሎች የማጣሪያ ውድድሮች ተካሂደዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም