የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ የመደመር ትውልድን ግንባታ እንዲደግፍ ጥሪ ቀረበ

320

አዲስ አበባ መጋቢት 14/20115 (ኢዜአ) የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ባለው ተቋማዊ አቅም የመደመር ትውልድን ግንባታ እንዲደግፍ ጥሪ ቀረበ።

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ መደመር የኢትዮጵያን እምቅ አቅም በማሰባሰብ ሀገርን ወደ ከፍታ ለማሻገር በለውጡ የተወለደ የፖለቲካ ዕይታና ማዕቀፍ መሆኑን ጠቅሰዋል።


 

መደመር ግቡ ያለፉ ጠባሳዎቻችንን ማከም፣ ችግርቻችንን በአገር በቀል እውቀት በጋራ መፍታት ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲሱ የመደመር ትውልድ መፅሃፋቸው የመደመር ትውልድ ከትናንት በመማር በጋራ ጥረታቸው ጠንካራዋንና የበለፀገች ኢትዮጵያን መገንባት እንዳለባቸው መክረዋል ብለዋል።


 

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም በበኩላቸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር እሳቤና የመደመር ትውልድ መጻህፍትን ሀገርና ዓለምን ለመጥ   ቀም በማሰብ ለንባብ እንዳበቁ ተናግረዋል።

መደመር ያለፉ ውስብስብ ሀገራዊ ችገሮችን በጋራ መፍታትን፣ ዓለም ቀፋዊ ትብብር ማጠናከርን የሚያስገነዘብ መሆኑንም ጠቅሰዋል።


 

ከመጻሕፍቱ ሽያጭ የሚገኘው ገንዘብ ለትውልዱ የሚጠቅሙ ፕሮጀክቶችን በማልማት ላይ እየዋለ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የመደመር ትውልድ መፅሐፍ ሲመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመፅሐፉ ሽያጭ የቱሪዝም ስፍራዎችን እና የወጣቶች የመዝናኛ ስፍራዎችን ለመገንባት እንዲውል መወሰናቸውን ሀላፊዋ አውስተዋል።


 

ዓለም አቀፉ ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብም የመደመር ትውልድን በመገንባት ረገድ ሚናውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ መፅሐፉን በመግዛት በኢትዮጵያ የልማት ስራዎች ላይ አሻራውን እንዲያሳርፍ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ሀላፊዋ ጥሪ አቅርበዋል።


 

የመደመር ትውልድ አቅምን አሰባስቦ አገርንና ዓለምን የመለወጥ ልህቀትን የሚሻና ለስኬቱ የሚተጋ  መሆኑን የተናገሩት በመፅሐፉ ላይ ዳሰሳ ያቀረቡት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት ዶክተር ምህረት ደበበ ናቸው።

የመደመር እሳቤ ዓለም አቀፋዊ መርሆን ያገናዘበ በመሆኑ ሁሉም የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ እንደ የአውዱ ሊጠቀምበት እንደሚችልም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም