"የመደመር ትውልድ" መጽሐፍን ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው

657


አዲስ አበባ መጋቢት 14/2015 (ኢዜአ)፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍን ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው።

"የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ የእንግሊዝኛ ቅጂ የሆነው "Generation Medemer"ን ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር በወዳጅነት ፓርክ ቁጥር ሁለት ነው እየተካሄደ ያለው። 

በመርሐ -ግብሩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዎች አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና  አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም እንዲሁም መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላትና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል። 

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም የመደመር ትውልድ የኢትዮጵያን ወደ ከፍታ የመሻገር ህልሞች የሚያሳካ መሆኑን ከመፅሐፉ ጠቅሰው አቅርበዋል። 

መርሐ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመጽሐፉ ምረቃ ላይ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች መደመር መጽሐፍን በመሸጥ ከሚገኘው ገቢ ለትውልዱ የሚጠቅሙ ፕሮጀክቶችን እንዲገነቡ ያቀረቡት ጥሪ አካል ነው ብለዋል። 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ምስጋኑ አርጋ በዚህ ወቅት፥ መደመር አዲስ ሀገርበቀል የፖለቲካ ለውጥ ዕሳቤ መሆኑን ጠቅሰዋል። 

የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሀገራዊ መግባባት ለማምጣት መፍትሔዎችን ያመላከተ ነው ብለዋል። 


አዲሱ የመደመር ትውልድ አቅሙን በማሰባሰብ ጠንካራዋን ኢትዮጵያን መገንባት እንዳለበት ተናግረዋል። 


የወጣቱን እምቅ እውቀትና ጉልበት ለሀገርና ለአህጉር ዕድገት መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም