በምዕራብ ወለጋ ዞን ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 13 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በምዕራብ ወለጋ ዞን ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 13 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ
ጊምቢ መጋቢት 14/2015 (ኢዜአ)፦ በምዕራብ ወለጋ ዞን ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 13 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ።
በዞኑ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ የተደረገው ከመጋቢት 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተሰራ የቦንድ ሽያጭና ስጦታ መሆኑም ተጠቅሷል ነው።
የዞኑ የኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ላሊሴ ሽብሩ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በቦንድ ሽያጭና በስጦታ 13ሚሊዮን 265ሺሕ 742 ብር ከተለያዩ ኅብረተሰብ ክፍሎች መሰበሰቡን ተናግረዋል፡፡
የዞኑ ነዋሪዎች የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ያልተቋረጠ ድጋፍ ሲያድረጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡
በዞኑ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረበትን 12ኛ ዓመት በማስመልከት የህዝብ ንቅናቄ ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝም አክለዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስከሚጠናቀቅ ድረስም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።
ኢዜአ ያነጋገራቸው የዞኑ ነዋሪዎች ግድቡ የህልውና ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፤ የግድቡ ግንባታ እስከሚጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን ድግፍ እንደሚያደረጉ ገልጸዋል፡፡
ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ እያደረጉ ካሉ የዞኑ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ሜቲ ጫሊ በበኩላቸው፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ቦንድ በመግዛት ድጋፍ ሲያድረጉ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
የጊምቢ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ኑሬ ጃማል በበኩላቸው ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውንና አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።