የረመዳን ጾም የፊታችን ሐሙስ ይጀመራል

አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ):- የ1444ኛው ዓመተ ሒጅራ የረመዳን ጾም የፊታችን ሐሙስ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።

ጾሙ ሐሙስ የሚጀመረው የረመዳን ወር ጨረቃ ዛሬ(ማክሰኞ) ባለመታየቷ እንደሆነም ገልጿል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ጾሙ ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ የአንድነት፣በጎ ነገር የማድረግ፣የመተዛዘንና የበረከት እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም