የሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው

291

ሀዋሳ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በሀዋሳ ከተማ እየመከሩ ነው ።

በመድረኩም “ድሎችን የማጽናትና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊና ታሪካዊ የአመራር ተልዕኮ” የሚል ሰነድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

ሰነዱን ያቀረቡት የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ አባልና በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ጽህፈት ቤት የፖለቲካና ሪዕዮተ ዓለም ዘርፍ ሃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ናቸው ።


 

የውይይቱ ዓላማ አመራሩ ነባራዊ ወቅታዊና ሀገራዊ ሁኔታን በመረዳት የተገኙ ስኬቶችንና አሁናዊ ሁኔታዎችን ተገንዝቦ ፈተናዎችን ወደ ድል ለመቀየር የሚያስችል ቁመና ላይ በመድረስ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን መፍጠር መሆኑን በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አሸናፊ ኤልያስ ተናግረዋል ።

እንዲሁም ዜጎች የሚያነሷቸውን ወቅታዊ ሁኔታዎች ተገንዝበው ብቁ አመራር የመስጠት አቅም እንዲፈጠሩ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑንም አስረድተዋል።


 

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኦርዲን በድሪና የቤኒሻንገል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሻድሌ ሀሴን መድረኩን እየመሩት ይገኛል።


 

በመድረኩም ከ450 በላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም