የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ሹመቶችንና ዓዋጆችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ

ሀዋሳ መጋቢት 12 /2015 (ኢዜአ)፦ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር ሁለተኛ የስራ ዘመን አራተኛ መደበኛ ጉባዔ የቢሮ ኃላፊዎችንና የዳኞች ሹመት አጸደቀ።

ምክር ቤቱ የቀረቡለትን ሶስት ዓዋጆችንም በማጽደቅ ነው የተጠናቀቀው።

በምክር ቤቱ ቀርቦ  ቀርቦ ሹመታቸው ከጸደቀው  የቢሮ ኃላፊዎችመካከል:-

 አቶ ማምሩ ሞኬ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ከበደ ገኖሌ የውሃ ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ አሰፋ ጉራቻ የሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ መኩሪያ መርሻዬ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም ዶክተር ዳዊት ሀዬሶ የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።


 

በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ደምሴ ዱለቻ አቅራቢነት ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አራት፣ ለሀዋሳ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስድስት፣ ለበንሳ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለት፣ ለሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስድስት፣ ለበንሳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 10 እና ለሀዋሳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሁለት ዳኞች ተሹመዋል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤት ዓዋጅ፣ የልማት ድርጅቶች አዋጅና የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ዓዋጆችን በማጽደቅ ጉባዔውን አጠናቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም