የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 8ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015 (ኢዜአ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 8 መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጕዳዮች ላይ ተወያ ውሳኔ ማሳለፉን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አስታውቋል


 

1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በመንግሥት ባለቤትነት የተያዙ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ረቂቅ እዋጅ ላይ ሲሆን የቀረበው ረቂቅ አዋጅም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የኮርፖሬት አስተዳደር ሥርዓት ግልፅነትን እና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ እንዲሆን፣ የኮርፖሬት ፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓታቸውን በማዘመን ተወዳዳሪነታቸውን እና ውጤታማነታቸውን ማጠናከር የሚገባ በመሆኑ፣ ትርፋማነታቸውን በማይጎዳ መልኩ የማህበራዊ አገልግሎት ግዴታቸውን በውጤታማነት መወጣት እንዲችሉ የልማት ድርጅቶች ያለባቸውን የዕዳ ማሻሻል የሚያስችል በመሆኑ በአጠቃላይ በአገር ኢኮኖሚ እድገት ላይ የጎላ አስተዋጽኦ እንዲያበረ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለም ቤቱ ቀርቧል። ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል እንዲጸድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው ኢትዮጵያ ከሎግዘምበርግ መንግስት እንዲሁም ከስዊዝ ኮንፌዴሬሽን ጋር ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት እና የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል ያደረገቻቸውን ስምምነቶችን ለማጽደቅ በቀረቡ ረቂቅ አዋጆች ላይ ነው ኢትዮጵያ ከሁለቱ መንግስታት ጋር ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት እና የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል ያደረገቻቸው ስምምነቶች የሁለቱ አገራት ባለሀብቶች ሃብታቸውን በአገራችን ኢንቨስት እንዲያደርጉ በማበረታታት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው ከመሆኑም በላይ ባለሃብቶቹ ለአንድ ገቢ ከአንድ ጊዜ በላይ ግብር እንዳይከፍ የሚያደርግ በመሆኑ ስምምነቶቹን ለማስጸደቅ ረቂቅ አዋጆች ተዘጋጅ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርበዋል። ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጆቹ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል እንዲጸድቁ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።

3. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ ደንብ ለማሻሻል በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው የኮርፖሬሽኑን የተፈቀደ እና የተከፈለ ካፒታል በማሻሻል የተቋቋመበትን ዓላማና ተልዕኮ ለማሳካት እንዲችል በተለይም በግንባታ ላይ ያሉ የባቡር መሰረተ ልማቶች እንዲጠናቀቁ የተጠናቀቁትም ወደ ስራ እንዲገቡ፤ በቀጣይ ለሚገነቡ የባቡር መሠረተ-ልማቶች የተሻለ አቅም እንዲኖረው የተፈቀደ ካፒታሉ ወደ ብር 221 ቢሊዮን ከፍ እንዲል በጥሬ ገንዘብና በአይነት የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ ብር 120 ቢሊዮን እንዲሆን ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም