የሀረሪ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እያካሄዱ ነው

ሀረር መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦የሀረሪ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማካሄድ መጀመራቸው ተገለጸ።

ውይይቱ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሠሞኑን ባካሄደው ውይይት ያሣለፋቸውን ውሣኔዎች፣ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑም ተመላክቷል፡፡


 

በመድረኩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ እንዲሁም የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኤሌማ አብበከር ፣የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ፣ የሀረሪ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንትና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሚስራ አብደላን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል።


 

በውይይት መድረኩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሠሞኑን ባካሄደው ውይይት ያሣለፋቸውን ውሣኔዎች የያዘ የውይይት ሠነድ አቅርበዋል፡፡

ውይይቱ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም