የኔ ያልነውን የጋራ ሀብት በማድረግና በማልማት አብረን ሠርተን እንበልጽግ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ - ኢዜአ አማርኛ
የኔ ያልነውን የጋራ ሀብት በማድረግና በማልማት አብረን ሠርተን እንበልጽግ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ መጋቢት 11/2015(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የኔ ያልነውን የጋራ ሀብት በማድረግና በማልማት አብረን ሠርተን እንበልጽግ ሲሉ መልዕክት አስተላለፉ።
ምርጥ ሀገር አለን ሲሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዓይናችንን ገልጠን ብንሠራ ለዓለም መስሕብ መሆን የሚችሉ በርካታ ቦታዎች በሀገራችን አሉ ብለዋል።
አካባቢን መቃኘትና መፈተሽ እንደሚገባም ገልጸው “የኔ ያልነውን የጋራ ሀብት እናድርግ፤ እናልማ፤ አብረን ተግተን ሠርተን እንበልጽግ ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።