የሲዳማ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

294


ሀዋሳ መጋቢት 11/2015 (ኢዜአ) .... የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።

የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ ለሁለት ቀናት ቆይታ የሚኖረው መሆኑ ተመላክቷል።

ጉባኤው በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሚቀርበውን የክልሉ መንግስት የሰባት ወራት የሥራ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጦና ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

 የተለያዩ አዋጆች ቀርበው ውይይት በማድረግ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም