የየመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር አህመድ አዋድ ቢን ሙባረክ አዲስ አበባ ገቡ

578

አዲስ አበባ መጋቢት 11/2015(ኢዜአ):- የየመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር አህመድ አዋድ ቢን ሙባረክ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።


 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል።


 

ዶክተር አህመድ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም