የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ 'የመደመር ትውልድ' መፅሐፍ ተመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ 'የመደመር ትውልድ' መፅሐፍ ተመረቀ

አዲስ አበባ መጋቢት 9/2015(ኢዜአ)፦የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ 'የመደመር ትውልድ' መፅሐፍ ተመረቀ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም 'መደመር' እና 'የመደመር መንገድ' የተሰኙ ሁለት መፅሐፍትን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል።
በዛሬው ዕለት የተመረቀው 'የመደመር ትውልድ' በአማርኛ፣ ኦሮምኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች የታተመ ነው።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የታደሙ ሲሆን የተለያዩ ምሁራን በመፅሐፉ ላይ ምሁራዊ ዳሰሳ አቅርበዋል።
ከዚህ ቀደም ለንባብ ከበቁት 'መደመር' እና 'የመደመር መንገድ' መፅሐፍት ሽያጭ የተገኘው ገቢ ለትምህርት ቤቶች ግንባታ እንዲውል መደረጉ ይታወሳል።
ዛሬ ከተመረቀው 'የመደመር ትውልድ' መጽሀፍ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በየክልሉ የሚገኙ ታሪካዊና የቱሪስት መስህብ የሆኑ ስፍራዎችን ለማደስ እንደሚውል ታውቋል።