36ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት ምስጋናና እውቅና ተሰጠ - ኢዜአ አማርኛ
36ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት ምስጋናና እውቅና ተሰጠ
አዲስ አበባ መጋቢት 5 ቀን 2015 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር 36ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት ምስጋናና እውቅና ሰጠ።
36ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት እውቅና የመስጠት መርሀግብር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት በስካይላይት ሆቴል ተካሂዷል።
በቱርኪዬ ተከስቶ በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ የነፍስ አደን ስራ ለመስራት ከኢትዮጵያ ለሄደው ቡድንም እውቅና ተሰጥቷል።
በመርሀግብሩ ላይ 36ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት እውቅና የተሰጠ ሲሆን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን ጨምሮ ለበርካታ ተቋማት እውቅና ተሰጥቷል።
የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 11 እና 12 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል።