የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮፐንሀገን ወደ አዲስ አበባ ሳምንታዊ የእቃ ጭነት አገልግሎት በረራ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮፐንሀገን ወደ አዲስ አበባ ሳምንታዊ የእቃ ጭነት አገልግሎት በረራ ጀመረ
አዲስ አበባ መጋቢት 6/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዴንማርክ ኮፐንሀገን ወደ አዲስ አበባ ሳምንታዊ የእቃ ጭነት አገልግሎት በረራ መጀመሩን አስታወቀ።
አየር መንገዱ በረራው ከመጋቢት 3/2015 ጀምሮ እየሰራበት መሆኑን ገልጿል።
በረራው የሚደረገው በቅርቡ ከመንገደኛ ወደ እቃ ጭነት አገልግሎት በተቀየረው ቦይንግ 767-300F አውሮፕላን መሆኑንና በእያንዳንዱ በረራም እስከ 45 ቶን ያህል ጭነት እንደሚጓጓዝ ተጠቅሷል ።
አዲሱ የጭነት አገልግሎት በአውሮፓ እና በተቀረው ዓለም ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ እንደሚያሳልጥ አመልክቷል።
አየር መንገዱ በግንቦት ወር 2015 ዓ.ም ወደ ኮፐንሀገን ለመጀመር ካቀደው የመንገደኞች በረራ አገልግሎት ጋር ተዳምሮ ተጨማሪ የካርጎ አገልግሎት አቅም እንደሚፈጥርለትም ጠቁሟል።