ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ህዝቦች መካከል ያለው ትብብር እያደገ ነው - የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሃሙድ

አዲስ አበባ መጋቢት 5/2015 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ህዝቦች መካከል ያለው ትብብር እያደገ  መምጣቱን የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሃሙድ ተናገሩ።

በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ከሰላምና መረጋጋት ባለፈ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ያለው ትብብር እያደገ መምጣቱን የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሃሙድ ገለጹ፡፡

በሶማሊያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙክታር መሃመድ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ አቅርበዋል።

በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ከሰላምና መረጋጋት ባለፈ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ያለው ትብብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሃሙድ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ በዚህ ወቅት፣ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እያበረከተች ላለችው አስተዋፅኦ አመስግነዋል፡፡

አምባሳደር ሙክታር መሃመድ በበኩላቸው ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የተለያዩ እሴቶችን እንደሚጋሩ ነው የገለጹት፡፡

ሁለቱ ሀገራት በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ከሚያደርጉት ትብብር ባሻገር በሌሎች ዘርፎች ያለው የትብብር ልምድ ሊዳብር ይገባል ሲሉ መጥቀሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም