የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኬፕ ታውን ተጨማሪ በረራ ሊያደርግ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኬፕ ታውን ተጨማሪ በረራ ሊያደርግ ነው
አዲስ አበባ መጋቢት 5/2015 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኬፕ ታውን በሳምንት አራት ተጨማሪ በረራ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።
ተጨማሪ በረራውን መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚጀምር ገልጿል።
አየር መንገዱ በደቡብ አፍሪካ ከኬፕ ታውን ውጪ በጆሀንስበርግ የመደበኛ በረራ አገልግሎት እንደሚሰጥ ይታወቃል።
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት አየር መንገዱ ወደ ሁለቱ ከተሞች የሚያደርገውን በረራ አቋርጦ ነበር።
መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ ከተሞቹ የሚያደርገውን በረራ ዳግም መጀመሩ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ከ60 በላይ መዳረሻዎች እንዳሉት አስታውቋል።