ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳንን መረጋጋት እና ሰላም ለመደገፍ ቁርጠኛ ናት-ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ

464

አዲስ አበባ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳንን መረጋጋት እና ሰላም ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።


 

ለአንድ ቀን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ደቡብ ሱዳን ጁባ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና ከተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር ጋር መወያየታቸውን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪርን በደቡብ ሱዳን በቆየንበት ወቅት ለእኔ እና ለልዑካን ቡድኔ ላደረጉልን አቀባበል አመሰግናለሁ” ብለዋል።


 

“ከፕሬዝዳንት ኪር እና ከተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት ሪክ ማቻር ጋር ባደረግኩት ውይይት፣ ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳንን መረጋጋት እና ሰላም ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት አጋርቻለሁ” ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም