ቀጥታ፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ነገ ይጀመራል 

 

አዲስ አበባ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ)፦ ሶስተኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ሁለተኛ ዓመት የስራ ዘመን ሶስተኛ መደበኛ ጉባኤ ነገ ይጀመራል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባኤ ምከር ቤቱ የከተማ አስተዳደሩን የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም እና የተለያዩ አዋጆች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ የምክር ቤቱ የፕሬስ እና ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አዲስአለም እንቻለው ገልጸዋል። 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በሚካሄደው ጉባኤ የምክር ቤት አባላት፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እንደሚገኙበት  ከአዲስ አበባ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም