የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ዓመታዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

770

አዲስ አበባ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ)፦ የ2023 የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ዓመታዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ መጀመሩን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በጉባኤው ለአፍሪካ አባል አገራት ኤጀንሲው የሚያደርገውን ድጋፍና የቴክኒካዊ ትብብር አተገባበር ገምግሞ የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል።


 

በጉባኤው ላይ የኤጀንሲው ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የአባል አገራት ተወካዮችና፣ የአፍሪካ አገራት የዘርፉ የምርምርና የድጋፍ ብሔራዊ አስተባባሪዎች መገኘታቸው ተጠቁሟል።

ጉባኤው ከመጋቢት 4 እስከ 8/2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም