በደብረ ብርሃን ከተማ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ዘውዲቱ አደራው እና አትሌት ጫላ ከተማ አሸናፊ ሆኑ - ኢዜአ አማርኛ
በደብረ ብርሃን ከተማ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ዘውዲቱ አደራው እና አትሌት ጫላ ከተማ አሸናፊ ሆኑ
አዲስ አበባ መጋቢት 3/2015 (ኢዜአ)፦ በደብረ ብርሃን ከተማ ዛሬ ማለዳ ላይ በተካሄደው 16ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች አትሌት ዘውዲቱ አደራው፣ በወንዶች ደግሞ አትሌት ጫላ ከተማ አሸናፊ ሆነዋል።
በሴቶች በተደረገው የግማሽ ማራቶን ውድድር ከአማራ ፖሊስ የተገኙት አትሌት ዘውዲቱ አደራው እና እናትነሽ አላምረው አንደኛና ሁለተኛ ሆነው ሲያጠናቅቁ፤ የኢትዮ ኤሌክትሪክ አትሌት የሆነችው መሰረት ጎላ ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች።
በወንዶች በተደረገው የግማሽ ማራቶን ውድድር ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ የተገኘው አትሌት ጫላ ከተማ ውድድሩን በአንደኛነት ሲያጠናቅቅ፤ ከፌደራል ማረሚያ የተወከለው አትሌት ተሰማ መኮንን ሁለተኛ አንዲሁም ከኢትዮ ኤሌክትሪክ የተገኘው አትሌት ሀብታሙ አብዲ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል።