የግማሽ ማራቶን ውድድር በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የግማሽ ማራቶን ውድድር በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ መጋቢት 3/2015 (ኢዜአ)፦16ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው ።
በዚህ ውድድር ላይ ከሁለት ክልሎች 12 ክለቦች እና ተቋማት እንዲሁም በግል የሚወዳደሩ አትሌቶችን ጨምሮ በወንድ 190 ፣ በሴት 96 በድምሩ 286 አትሌቶች እንደሚሳተፉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል።