ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ መጋቢት 2/2015(ኢዜአ)፦ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሐግብር ዛሬ በሚካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል።
ኢትዮጵያ ቡና ከሐዋሳ ከተማ ከቀኑ 10 ሰአት በድሬዳዋ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ቡናማዎቹ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ሰባተኛ እንዲሁም ሐዋሳ ከተማ አራተኛ ደረጃን ይዟል።
በሌላኛው የ17ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሲዳማ ቡና ከሀዲያ ሆሳዕና ከምሽቱ 1 ሰአት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ሲዳማ ቡና በደረጃ ሰንጠረዡ 13ኛ፤ ሀዲያ ሆሳዕና 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
የፕሪሚየር ሊጉ 17ኛ ሳምንት መርሐግብር እስከ መጋቢት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ይቆያል።
የሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ35 ነጥብ ይመራል።
ባህር ዳር ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን በተመሳሳይ 30 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው በቅደም ተከትል ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ይዘዋል።
አርባ ምንጭ ከተማ፣ ኢትዮ-ኤሌትሪክና ለገዳፎ ለገዳዲ ከ14ኛ እስከ 16ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ።
የፕሪሚየር ሊጉን ከፍተኛ የግብ አስቆጣሪነት ቶጎዋዊው የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት መስመር ተሳላፊ ኢስማኤል ኦሮ- አጎሮ በ16 ግቦች ይመራል።
የወልቂጤ ከተማው ጌታነህ ከበደ በ12 እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማው ቢኒያም ጌታቸው በ8 ግቦች ይከተላሉ።