የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሴት አብራሪዎች ብቻ የተመራ በረራ ወደ ዛንዚባር አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሴት አብራሪዎች ብቻ የተመራ በረራ ወደ ዛንዚባር አደረገ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 29/2015 የኢትዮጵያ አየር መንገድ እየተከበረ ያለውን አለም አቀፉን የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ በሴት አብራሪዎች ብቻ የተመራ በረራ ወደ ዛንዚባር ማድረጉን አስታወቀ።
"እኔም የእህቴ ጠበቃ ነኝ" በሚል እየተከበረ ያለውን የዓለም የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ በሴት አብራሪዎች ብቻ የተመራ በረራ ወደ ዛንዚባር ማድረጉን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ112ኛ ግዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ47ኛ ግዜ በተለያዩ ሁነቶች በመከበር ላይ ይገኛል።