የአንጋፋው የሥነ ጽሑፍ መምህርና ሐያሲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

926

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 29/2015 የአንጋፋው የሥነ ጽሑፍ መምህርና ሐያሲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ።


 

በ1944ዓ.ም በደሴ ከተማ የተወለዱት ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው ከ1976ዓ.ም ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት፣ በተመራማሪነት በአማካሪነት፣ በትምህርት ክፍል ኃላፊነት በቦርድ አባልና እና በሌሎች የኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል።

ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን ‹‹የሥነ ጽሑፍ መሰረታውያን›› እና ‹‹ከበዓሉ ግርማ እስከ አዳም ረታ›› እና ሌሎች ሶስት መጽሐፍትን አሳትመዋል፡፡


 

ስርዓተ ቀብራቸው በዛሬው እለት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ተከናውኗል።

የአንጋፋው የስነ-ጽሑፍ ሰው ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው የአንድ ሴት ልጅና የሶስት ወንድ ልጆች

አባት ነበሩ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም