የሴቶች ቀን ሲታሰብ

1296

የሴቶች ቀን ሲታሰብ የሰው ልጅ ሕይወትን ቀላል ባደረጉ የፈጠራ ስራዎቻቸው የምናስባቸው እንስቶች በቀዳሚነት ይነሳሉ።

በተለያዩ መስኮች አሻራቸውን ያሳረፉ እንስቶች ቁጥራቸው ከፍተኛ ቢሆንም በዚህ ጽሑፋችን ግን በኬሚስትሪና ፊዚክስ ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃ ባበረከቱት አስተዋጽኦ በኖቤል ሽልማት እውቅና የተሰጣቸውን የየዘመኑ ፈርጦች እንዳስሳለን።

ከነዚህ ፈርጦች መካከል በኬሚስትሪ ዘርፍ የኖቤልን ሽልማትን ከሴቶች ቀዳሚ በመሆን በቀዳሚነት ያሸነፉት ሜሪ ኩሪ ይወሳሉ።

ይልቁንም እ.አ.አ በ1903 በኬሚስትሪ ዘርፍ የተቀበሉትን የኖቤል ሽልማት በድጋሚ በ1911 በመሸለም ብቸኛነት ስማቸው ይነሳል።

በ1967 በፖላንድ ዋርሶ የተወለዱት ማሪ ኩሪ ለዘመናዊው የሳይንስና ኬሚስትሪ ዘርፍ ውለታን ከዋሉ ስመጥር ተመራማሪዎችና በጨረራ ህክምና ፈጠራ የዘርፉ ፈር ቀዳጅ በመሆን የአለምን የራዲዮአክቲቪቲ እይታን የቀየሩ ጀግና ናቸው።


 

የሜካኒካልና ኤሮስፔስ ተመራማሪዋ ፍራንሲስ አርኖልድ ደግሞ በህክምናናና በታዳሽ ኃይል ዘርፍ አሻረቸውን በጉልህ ካኖሩ ተመራማሪዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
አሜሪካዊቷ ፍራንሲስ ለታዳሽ ኃይል እና ለፋርማሲ አገልግሎት የሚውል አዲስ ኢንዛይም በምርምር በማግኘት በዘረፉ አሻራቸውን አኑረዋል። ለዚህም አስተዋጽኦዋ እ.አ.አ በ2018 በኬሚስትሪ ዘርፍ የኖቤልን ሽልማት አሸንፈዋል። 

የኤድስን ስርጭትን በመከላከል ረገድ ሰፊ አበርክቶ ያላቸው የህክምና ተመራማሪዋ ፍራንሶዝ ባሪሲኖሲም የሴቶች ቀን  ሲታሰብ ከሚወሱ አንስቶች አንደኛዋ ናቸው። ባሪሲኖሲ የኤች አይቪ ኤድስን ከገዳይ በሽታነት መታከምና መቆጣጠር ወደ ሚችል በሽታነት ለመቀየር የኤች አይቪ  ኤድስ ምርመራን በማላቅ ረገድ ሚናቸው የጎላ እንደሆነ ይወሳል።

በ1947 በፓሪስ ከተማ የተወለዱት ባሪሲኖሲ “ሳይንስን ለሰው ልጆች ጥቅም እንዲውል እንሰራለን” በሚለው አባባላቸው ይታወቃሉ። ኤድስን በመከላከል ላደረጉት አስተዋጽኦም በፊዚዮሎጂ/ሕክምና ዘርፍ እ.አ.አ በ2008 የኖቤል ሽልማትን አግኝተዋል።

ያለ ህክምና ትምህርት የሚሊዮኖችን ሕይወት በታደገው የወባ በሽታ መከላከያ ፈጠራቸው አለም እውቅና የተሰጣቸው ቱ ዩዩ በሴቶች ቀን የምናመሰግናቸው ሌላኛዋ ተመራማሪ ናቸው።

ቻይናዊቷ ቱ ዩዩ ባህላዊውን የወባ በሽታ መከለከያ ህክምና ወደ ዘመናዊ በመቀየርና በማስተዋወቅ ነው ስመ ገናና የሆኑት።


 

የወባ በሽታን በመከላከል ረገድ በአለም አቀፍ ደረጃ ጉዙፍ አሻራቸውን ላስቀመጡት ተመራማሪ ባለውለታነት እ.አ.አ በ2015 በፊዚዎሎጂ/ ህክምና ዘርፍ ሳይንስ ምድብ የመጀመሪያዋ ቻይናዊት በመሆን የኖቤል ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
 
የሰው ልጆችን ሕይወት ካቀለሉ አለም አቀፍ ፈጠራዎች መካከል የተጠቀሱትን ጨምሮ በሌሎችም ዘርፎች የሴቶች ተሳትፎ የጎላ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም