ቀጥታ፡

የፓኪስታን ባለሃብቶች የአንድነት ፓርክን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 29/2015 የፓኪስታን ባለሃብቶች የአንድነት ፓርክን እየጎበኙ ይገኛሉ።

የፓኪስታን ንግድና ኢንቨስትመንት ልዑክ በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት  አማራጮችን ለመጎብኘት ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ይታወቃል።

ለልዑካን ቡድኑ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ አማካኝነት በኢትዮጵያ የሚገኙት የኢንቨስትመንት አመራጮች ላይ ገለጻ መደረጉም የሚታወስ ነው።


 

ልዑኩ በትናንትናው ዕለት የቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን መጎብኘታቸው ይታወሳል።

በዛሬው ዕለትም የአንድነት ፓርክን በመጎብኘት ላይ ሲሆኑ በቀጣይም ሌሎች የቱሪስት መዳረሻዎችን እንደሚጎበኙ ተገልጿል።

በጉብኝቱ ልዑካኑን ጨምሮ በፓኪስታን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን  አምባሳደር  ጀማል በከር እና የኢንቨስትመንት  ኮሚሽን የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የንግድ እና የኢንቨስትመንት ሉዑኩ በመቀጠል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየምን ይጎበኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም