ቀጥታ፡

ስምንተኛው ዓለም አቀፍ የአበባ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ኤክስፖ ተከፈተ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 29/2015 ስምንተኛው ዓለም አቀፍ የአበባ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ (ሆርቲ ፍሎራ ኢንተርናሽናል) ኤክስፖ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፍቷል።                 

የግብርና  ሚኒስትር  ግርማ አመንቴ(ዶ/ር)፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና የኢትዮጵያ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራችና ላኪዎች ማህበር የቦርድ ሊቀ-መንበር አቶ ነጋ መኳንንት ኤክስፖውን በይፋ ከፍተዋል።


 

“ሆርቲ ፍሎራ ኤክስፖ” በሚል ስያሜ ለሶስት ቀናት በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ኤክስፖ 89 የአገር ውስጥ እና የውጭ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።


 

ዓለም አቀፍ የአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች እና አቅራቢዎች ከኢትዮጵያ የዘርፉ ተዋናዮች ጋር ትስስር እንዲፈጥሩ ማስቻል የኤክስፖው ዋነኛ አላማ እንደሆነ ተነግሯል።

በኤክስፖው በማዳበሪያ አቅረቦት፣ በኬሚካል፣ በግሪን ሀዉስ፣ በግብርና እቃዎች እንዲሁም በአግሮ ሎጂስቲክስ አገልግሎት  ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች እና አማካሪዎች እንደሚሳተፉ ተመልክቷል።


 

የኢትዮጵያ የአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራችና ላኪዎች ማህበር ከ’ኤችፒፒ’ ኤግዚቢሽን ጋር በመሆን ኤክስፖውን በጋራ አዘጋጅተውታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም