በፕሪሚየር ሊጉ ድሬዳዋ ከተማ ሲዳማ ቡናን በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል - ኢዜአ አማርኛ
በፕሪሚየር ሊጉ ድሬዳዋ ከተማ ሲዳማ ቡናን በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል
አዲስ አበባ(ኢዜአ) የካቲት 28/2015 በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ16ኛ ሳምንት መርሐግብር ድሬዳዋ ከተማ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 0 በማሸነፍ ወሳኝ ሶሰት ነጥብ አግኝቷል።
በድሬዳዋ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ያሬድ ታደሰ እና አቤል አሰበ ለድሬዳዋ ከተማ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ውጤቱንም ተከትሎ ድሬዳዋ ከተማ ነጥቡን ወደ 21 በማሳደግ ከነበረበት 13ኛ ወደ 10ኛ ደረጃ መምጣት ችሏል።
በአንጻሩ ሲዳማ ቡና በ19 ነጥብ ከነበረበት 11ኛ ደረጃ ወደ 12ኛ ዝቅ ብሏል።
በሌላኛው የ16ኛ ሳምንት መርሐግብር ከምሽቱ 1 ሰአት የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተከታዩ ኢትዮጵያ መድን ጋር በድሬዳዋ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።