ቀጥታ፡

አንጋፋው የሥነ ጽሑፍ መምህር እና ሐያሲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 28/2015 አንጋፋው የሥነ ጽሑፍ መምህር እና ሐያሲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።


 

ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን “የሥነ ጽሑፍ መሰረታውያን” እና “ከበዓሉ ግርማ እስከ አዳም ረታ” የሚሉትን ለሥነ ጽሑፍ ትምህርት አጋዥ መጻሕፍት ጨምሮ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎችን አሳትመዋል።

ምሁሩ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥነ ጽሑፍ ትምህርት ክፍል በሥነ ጽሑፍ መምህርነት እና አማካሪነት እያገለገሉ እንደነበር የሙያ ባልደረቦቻቸው መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።


 

በቅርቡም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሰውመሆን ፊልሞች ጋር በመተባበር ለሚሠራው "ፍቅር እስከ መቃብር" ባለ48 ክፍል የቴሌቪዥን ድራማ ሙያዊ ሐሳባቸውን አካፍለው እንደነበርም ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም