ስድስተኛው ዙር የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ስልጠና መጋቢት 4 ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
ስድስተኛው ዙር የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ስልጠና መጋቢት 4 ይጀመራል
አዲስ አበባ(ኢዜአ) የካቲት 28/2015 ስድስተኛው ዙር የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ስልጠና መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገለጸ።
የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ስልጠናውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በስልጠናው ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተወጣጡ ከ15 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እንደሚሳተፉ አቶ ታዬ ገልጸዋል።
በጎ ፈቃደኞቹ ስልጠናቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች በመሰማራት በተለያዩ ዘርፎች ነጻ አገልግሎት እንደሚሰጡ አመልክተዋል።
የበጎ ፈቃድ ሰልጠናው ለአንድ ወር የሚቆይ ሲሆን በስራ ፈጠራ፣ ስነ ልቦና እና ተጓዳኝ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑም ተገልጿል።
ባህር ዳር፣ ጅማ፣ ዋቻሞ እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲዎች ስልጠናው የሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ናቸው።