አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ በአውሮፓ ሕብረት ድጋፍ በጋምቤላ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ለመጎብኘት ጋምቤላ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ በአውሮፓ ሕብረት ድጋፍ በጋምቤላ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ለመጎብኘት ጋምቤላ ገቡ
ጋምቤላ ኢዜአ የካቲት 28/2015፦ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ በሕብረቱ ድጋፍ በጋምቤላ ክልል በመከናወን ላይ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ለመጎብኘት ጋምቤላ ከተማ ገቡ ።
አምባሳደሩ ጋምቤላ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ተድርጎላቸዋል ።
አምባሳደሩ በሚኖራቸው ቆይታ በህብረቱ ድጋፍ በክልሉ በጤናና ሌሎች የልማት ዘርፎች እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን የሚጎበኙ ሲሆን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ከሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩም ተመልክቷል።
በሕብረቱ ድጋፍ የጤናዉን ዘርፍ ለማጠናከር የተገዙ የተሽከርካሪዎችና ቁሳቁሶች ደጋፍ ርክክብ እንደሚያደርጉም የኢዜአ ሪፖርተር ከስፍራው ዘግቧል።