ቀጥታ፡

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሐዋሳ ከተማ ለገጣፎ ለገዳዲን 1 ለ 0 አሸነፈ 


አዲስ አበባ(ኢዜአ) የካቲት 27/2015 በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት  መርሐግብር ሐዋሳ ከተማ ለገጣፎ ለገዳዲን 1 ለ 0 ረቷል።

በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በረከት ሳሙኤል በ43ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ለሐዋሳ ከተማ ሶስት ነጥብ አስገኝታለች።

ውጤቱንም ተከትሎ ሐዋሳ ከተማ ነጥቡን ወደ 24 በማሳደግ ከሰባተኛ ወደ አራተኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።

ተጋጣሚው ለገጣፎ ለገዳዲ በስድስት ነጥብ በነበረበት የመጨረሻ 16ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በሌላኛው የ16ኛ ሳምንት መርሐግብር ከምሽቱ 1 ሰአት ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ዲቻ በድሬዳዋ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም