ቀጥታ፡

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ 


አዲስ አበባ(ኢዜአ) የካቲት 27/2015 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሐግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ሁለተኛው ዙር የፕሪሚየር ሊግ ውድደር ከትናንት በስቲያ መጀመሩ ይታወቃል።

በ16ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ውሎ ለገጣፎ ለገዳዲ ከሐዋሳ ከተማ ከቀኑ 10 ሰአት እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ዲቻ ከምሽቱ 1 ሰአት በድሬዳዋ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። 

ነገ የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ከያዘው ኢትዮጵያ መድን ጋር ከምሽቱ 1 ሰአት የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

ከሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ቀደም ብሎ ከቀኑ 10 ሰአት ላይ የሲዳማ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ ጨዋታ ይደረጋል።

በተያያዘ ዜና በድሬዳዋ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ሜዳው በመበላሸቱ ከትናንት በስቲያ መካሄድ የነበረበት የአርባ ምንጭ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ ጨዋታ ሐሙስ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም 11 ሰአት እንደሚደረግ የውድድር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም