የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ስም ቅርንጫፍ ከፈተ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ስም ቅርንጫፍ ከፈተ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 25/2015 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢሾፍቱ ከተማ በክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ስም ቅርንጫፍ ዛሬ ከፍቷል።
ባንኩ በቢሾፍቱ ከተማ ድሬ ጂቱ ቀበሌ በክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ስም የከፈተውን “አሊ ቢራ ቅርንጫፍ’’ የሚል ስያሜ ሰጥቶታል።
የቀድሞው አባ ጋዳ በየነ ሰምባቶ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት ወጋየሁ ገብረማርያም ቅርንጫፉን መርቀው ከፍተዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የባንኩ የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።