አዳማ ከተማ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
አዳማ ከተማ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 20/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ሀዋሳ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቢንያም አይተን በ54ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት እና ናይጄሪያዊው የሀዋሳ ከተማ ተከላካይ ቺኩውቡካ አንቶኒ በ84ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በሊጉ ሁለተኛ ድሉን ያስመዘገበው አዳማ ከተማ በዘጠኝ ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ በአምስት ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ሀዋሳ ከተማ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ አለው።