ቀጥታ፡

በመርሲሳይድ ደርቢ ኤቨርተን እና ሊቨርፑል ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 20/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ኤቨርተን እና ሊቨርፑል አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዶምኒክ ስቦዝላይ በአምስተኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፈው ጎል ሊቨርፑል መሪነቱን ይዟል።

የሊቨርፑሉ ተከላካይ ጀርሚ ፍሪምፖንግ በ25ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ ያስቆጠረው ግብ ኤቨርተንን አቻ አድርጓል።


በሁለተኛው አጋማሽ ሊቨርፑል ለማሸነፍ ጫና ፈጥሮ ቢጫወትም አልተሳካለትም።

ውጤቱን ተከትሎ ሊቨርፑል በ22 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። ወደ ሊጉ አናት የመጠጋት እድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

ኤቨርተን በ17 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም