ቀጥታ፡

የኦሮሚያ ክልል የባህል ስፖርቶች ውድድርና የባህል ፌስቲቫል መካሄድ ጀመረ

‎ሻሸመኔ፤ ህዳር 20/2019 (ኢዜአ)፡- የኦሮሚያ ክልል 32ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድርና 19ኛው የባህል ፌስቲቫል በሻሸመኔ ከተማ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።

በሻሸመኔ ከተማ መካሄድ የጀመረው የኦሮሚያ ክልል 32ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 19ኛው የባህል ፌስቲቫል፣ ባህል፣ ስፖርትና ማኅበራዊ አብሮነትን የሚያጠናክር መድረክ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ መርሐ ግብር በስምንት ቀናት ቆይታው ከጨዋታ ሜዳ እና ከመድረክ ትዕይንት ባሻገር የእርስ በርስ ትስስር የሚያጎለብትና የትውልድ ቅብብሎሽን የሚያጸና ሰፊ እሴት መሆኑም እንዲሁ።

ሻሸመኔ ከተማ ላይ መካሄድ በጀመረው የባህል ስፖርት ውድድርና ፌስታቫል ላይ ከመላው ኦሮሚያ የተወጣጡ የባህል ስፖርት ተወዳዳሪዎች በ10 የውድድር ዘርፎች እንደሚሳተፉ ታውቋል።

‎በባህል ስፖርትና ፌስቲቫሉ ላይ ደግሞ የየአካባቢው የባህል አልባሳት፣ ባህላዊ ምግቦች፣ ባህላዊ መገልገያ ቁሶች፣ ውዝዋዜዎችና የተለያዩ መገለጫዎች ለዕይታ ይቀርባሉ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኦሮሚያ ባህልና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ቢያን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም አባ ገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

መርሃ ግብሩ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ህዳር 27 ቀን 2019 ዓ.ም ለስምንት ቀናት እንደሚቆይ ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም