በአፍሪካ የባህል መድሃኒትቶች ትኩረት እየሰጣቸው ነው

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 25/2012(ኢዜአ) በአፍሪካ የባህል መድሃኒትቶች ትኩረት እየሰጣቸው መሆኑን በዓለም ጤና ድርጅት የአፍርካ ተወካይ ዶክተር ማትሺዲሶ ሞኤቲ ተናገሩ።

የባህል መድሃኒቶች ከጥንት ጀምሮ ጥቅም ላይ በመዋል ውጤት ተገኝቶባቸዋል አሁንም ተጠናከሮ ቀጥሏል ተብሏል።

በየዓመቱ ነሃሴ 25 ታስቦ የሚውለው የአፍሪካ የባህል መድሃኒት ቀን ዛሬ ሲከበር ላለፉት 20 ዓመታት በጤና ስርዓት ውስጥ ያሳየው ተቀባይነትና ያመጣው ለውጥ ታስቧል።

የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቢሮ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳለው የባህል መድሃኒቶች ለዘመናት አፍሪካውያንን የጠቀመ እና አሁንም የቀጠለ በመሆኑ በዓለም አቅፍ ገበያ ለሽያጭ ሊቀርብ ይገባል።

በተለይ ደግሞ ኮቪድ 19 ወረርሺኝ ስጋት በሆነበት በዚህ ጊዜ የአፍሪካ የባህል መድሓኒት ፍቱን ሊሆን እንደሚችል ውይይት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል ዶክተር ማትሺዲሶ።

በባህል መድሃኒቶች ላይ የሚደረገው ጥናት እንዲጠናከርና ጥናቱም ውጤታማ ሆኖ ከተገኘ ለማምረት ፈጣን ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

ይህንንም የዓለም ጤና ድርጅትና የአፍሪካ በሽታ መከላከል ማዕከል የሚደግፉት መሆኑን አረጋግጠዋል።

በአህጉሪቱ የባህል መድሓኒት ትኩረት እያገኘ መሆኑን የጠቀሱት ተወካይ በዚህ ወቅት 40 አገራት የባህል መድሃኒት ፖሊሲ አላቸው ብለዋል።

አገራቱ አብዛኞ የባህል መድሃኒትን ከብሔራዊ የጤና ፖሊሲ አጋር አቀናጀተው አስፈላጊ የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋታቸውንም ገልጸዋል።

በአፍሪካ 24 የከፍኛ ትምህርት ተቋማት የባህል መድሃኒት ላይ ያተኮረ ኮርስ ለፋርማሲና ሕክምና ተማሪዎች እየሰጡ መሆኑንም ነው የጠቀሱት።

ለአብነትም ጋና፣ ማሊና ደቡብ አፍሪካ ለባህል መድሃኒት አምራቾች የኢንሹራንስ ስርዓት የዘረጉ አገራት መሆናቸውን በመግለጫው ተመልክቷል።

የባህል መድሃኒት ለበርካታ አገሮች የጤና ስርአት አጋዥ በመሆን ለምእተ አመታት መዝለቁ ይታወቃል።

የዓለም ጤና ድርጅት ባህላዊ መድሃኒቶች በጥንቃቄና በተጠና መልኩ ለህክምና አገልገሎት እንዲውሉ ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም