የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም ምክር ቤት ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 21/2012(ኢዜአ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም ምክር ዛሬ ተመሰረተ።

በምስረታው ስነስርዓት ላይ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና ከሁሉም ክፍለከተሞች የተወጣጡ ባለድርሻ አከላት ተገኝቷል።

የምክር ቤቱ መመስረት ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ ለከተማዋ እድገትና ብልጽግና ወሳኝ መሆኑን ተገልጿል።

ምክር ቤቱ በወረዳ ደረጃ 300፣ በክፍለ ከተማ 400 እና በከተማ ደረጃ 500 አባላት የሚኖሩት ሲሆን፣ በከተማዋ እየተፈጸሙ ያሉ የወንጅል ድርጊቶችን በቅንጅት ለመፍታት ያስችላል ተብሏል።

ኪዘህ ባለፈ አዲስ አበባ ከተማ የዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ በመሆኗ ምክር ቤቱ ሰላምን የማረጋገጥ ተግባር ወሳኝ ተግባር እንዳለው ነው የተገለጸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም