በናይጀሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ገዙ - ኢዜአ አማርኛ
በናይጀሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ገዙ
ነሃሴ 21/2012( ኢዜአ) በአቡጃ ናይጀሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቦንድ መግዛታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በአቡጃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢፌዲሪ ኤምባሲ ባልደረቦች ባካሄዱት የቦንድ ግዥ ፕሮግራም 14000 /አስራ አራት ሺህ / የአሜሪካን ዶላር ግዥ ፈጽመዋል።
“ድጋፋችን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድባችንን ለማጠናቀቅ'' በሚል መሪ ቃል የቦንድ ሽያጭ መርሃ-ግብር በይፋ ተጀምሯል።
የግድቡ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስ በሁሉም ዘርፍ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በቦንድ ግዢ መርሃ-ግብሩ የተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን ቃል መግባታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።