ቀጥታ፡

አገር የመለወጥ ውጥን ከራስ መጀመር አለበት

አዲስ አበባ ነሀሴ 20/2012 ( ኢዜአ) አገር የመለወጥ ውጥን ከራስ መጀመር እንዳለበት ወጣቶች አስታወቁ ፡፡

ዓለም አቀፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከትምህርት ገበታቸው የተለዩ ተማሪዎች እንዲሁም ስራቸውን በቤታቸው እንዲከውኑ የታዘዙ ሰራተኞች አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦችን እንዲያፈልቁ ዕድል ፈጥሯል።

ለወቅታዊ ችግር ከንክኪ ነጻ መገልገያ ቁሳቁስን ከመፍጠር ጀምሮ ለወቅታዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ የሚሆኑ ሀሳቦችም እየፈለቁ ይገኛሉ።

ከሕዝቧ ከ74 በመቶ በላይ ወጣት በሆነባት ኢትዮጵያ ችግር ፈቺ የፈጠራ ሀሳቦች ያላቸውን ወጣቶች በማበረታታት ወደ ተግባር እንዲገቡ የማድረግ ጠቀሜታው አያጠያይቅም።

ወጣቱን በአመለካከት፣በዕውቀትና በክዕሎት ብቁና ተወዳዳሪ ማድረግ አገሪቷ ልትደርስበት ለምትፈልገው ብልጽግናም ወሳኝ ነው።

በኢትዮጵያ በተለያዩ የስራ መስኮች ተሰማርተው የሚንቀሳቀሱ ታታሪ ወጣቶች የመኖራቸውን ያህል በሱስና በአልባሌ ነገሮች በዋዛ ፈዛዛ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉም ቀላል የሚባሉ አይደሉም።

ወጣቶች ያላቸውን እውቀትና ክህሎት ተጠቅመው ጠንካራ አገረ-መንግስት የመገንባት ኃላፊነታቸውን የሚወጡት ቅድሚያ ራሳቸውን ማወቅና መቀየር ሲችሉ መሆኑ እሙን ነው። 

ይህን እውነታ በተግባር ለማሳየት ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች፣ሃይማኖት፣ባህልና ልምድ የተውጣጡና ለአንድ ዓላማ የቆሙ ወጣቶች ሀሳባቸውን ወደ ተግባር ለመለወጥ በጎ አድራጎት ድርጅት መስርተው ወደ ስራ ገብተዋል።

‘’የኢትዮጵያ ካላድሪዮ ወጣቶች’’ የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ድርጅት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ህጋዊ ሰውነት አግኝቷል።

ድርጅቱን ለመመስረት ለሶስት ዓመታት ‘’ላይ ታች’’ ሲሊ የነበሩት ወጣቶች የያዙት ራዕይ ከራሳቸው ፣ ከቤተሰቦቻቸው፣ ከጓደኞቻቸው፣ ከአካባቢያቸው አልፎ አገርን በአስተሳሰብ መቀየር ነው።

‘’አገር መለወጥ ከራስ ይጀምራል’’ የሚል ጠንካራ እምነት ያላቸው እነዚህ ወጣቶች፣ ማንኛውም ሰው ለአገሩ መልካም ነገር መስራት የሚችለው ራሱን በእውቀት፣በስነ-ምግባርና በአመለካከት የተሻለ ሲያደርግ ብቻ ነው ይላሉ።

 በዘመነ ‘’ሉአላዊነት’’ በኢትዮጵያ መጤ ባህሎች ስር ሰደው በተስፋፋበት ፣ወጣቱ የራሱን ባህልና ወግ ወደ ኋላ ብሎ ውጭውን በሚያማትርበት ጊዜ ‘’ ከራስ የጀመረ አገር የመለወጥ ውጥን''ይዘው የመጡበት ምክንያት ምን ይሆን?

''አገር የራሷ የሞራል ልዕልና አላት ማናችንም እንደልባችን እየተነሳን ልንቀይራት የምንችል ነገር አይደለም።ስለዚህ ምንድነው ማድረግ ያለብን ብለን የተነሳነው ከአገር በፊትም ከማንም በፊት ራሳችንን መለወጥ አለብን በሚል ነው የምትለን ተዋህዶ አለሙ የሶስተኛ አመት የኮምፒዩተር ሳይንስ ተማሪ ናት፡፡ 

የሶስተኛ አመት  የአካውንቲንግ ተማሪው ኤርሚያስ አለነ በበኩሉ አገር የሚለወጠው በወጣቶች ነው  ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት  ወጣቶች ደግሞ አገርን እንዳይለውጡ ሳንካ የሆኑባቸው ጉዳዮች ለመፍታት የበኩሉን  ለማበርከት መስራቱኝን በመጠቆም፡፡

''አንድ አገር ማንም ተነስቶ የሚለውጣት ወይም የሚቀይራት አይደለችም መጀመሪያ ራሳችንን መቀየር አለብን ራሳችንን ስንቀይር አካባቢያችን ያሉ ሰዎችን መቀየር አለብን” የአብጸጋ አስፋው የማርኬቲንግ ማኔጅመንት የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ነው፡፡

''የኢትዮጵያ ካላድሪዮ ወጣቶች’’ዋና ዓላማ የበርካታ ወጣቶችን ማህበራዊ፣ ስነ ልቡናና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በመፍታት የተሻለች አገር መገንባት መሆኑን ወጣቶቹ ይናገራሉ።

‘’የወጣቶች ዋነኛ ችግሮች ናቸው ብለን ለለየናቸው ጉዳዮች መፍትኤ ለማበጀት እንተጋለን’’ ነው ያሉት።

በየትምህርት ቤቶቹ የስፖርት ክለቦችን ከማቋቋምና ጠንካራ የተማሪዎች ህብረት ከመፍጠር ባለፈ በበጎ ፍቃድ አገልግሎት የአገርን ዳር ድንበር የመጠበቅ ተግባራትን ማከናወን የወጣቶቹ ሀሳቦች ናቸው።

''ሁሉም ወጣት መሆን የሚፈልገውን በቮለንተሪዝም የሚያገለግልበት ነው”የሚለን   የአብጸጋ አስፋው የማርኬቲንግ ማኔጅመንት የመጀመሪያ ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነው ፡፡

''አርበኝነት ወይም አገር ወዳድነት የሚለውን ሀሳብ በማምጣት ተማሪዎች ለምን በትርፍ ጊዜያቸው ከተማ ውስጥ ያሉትን እንቅስቃሴዎች አያግዟቸውም።ተዋህዶ አለሙ የሶስተኛ አመት የኮምፒዩተር ሳይንስ ተማሪ ሁላችንም ትርፍ ግዜያችን ሌሎችን መርዳት ይኖርብናል ብሏል፡፡

 መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ግለሰቦችና ተቋማት በሀሳብ፣ በገንዘብና በጉልበት ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል።

''ዕቅዳችን ከታችኛው የትምህርት ቤት እርከን ጀምሮ እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ ባለው ላይ ለመስራት ነው። ከሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንሻለን የሚለው ኤርሚያስ አለነ የሶስተኛ አመት የአካውንቲንግ ተማሪ ነው

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም