ቀጥታ፡

''ዓላማችን ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ንጋትን ማብሰር ነው''-ጠቅለይ ሚኒስትር ዓቢይ

አዲስ አበባ ነሀሴ 20/2012 ( ኢዜአ) ''ዓላማችን ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ንጋትን ማብሰር ነው'' ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንዳመለከቱት፤ የመንግሥታቸው ዋነኛ ዓላማ ለኢትዮጵያውያን ሕይወት መሻሻል መሥራት ነው፡፡

''ግባችን ለሁሉም ሕዝብ ብሩህ ቀን እንዲመጣለት ማስቻል ነው። እንዳንዱ ዜጋ በሀገሩ ደስታን፣ በሀገሩ ምቾትን፣ በሀገሩ ተስፋን እንዲጨብጥ የማድረግ ጉዟችን የማለዳዋን ጸሐይ ተከትሎ ሙቀትና ፍካቱ እየጨመረ ብሩህ የሆነው'' ሲሉም አክለዋል፡፡

''የብልጽግና መንገድ የማለዳውን ጀምበር ተከትሎ እየፈካ መጥቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ፤የብርሃን ጸዳሎቹ ሙቀትና ፍካትን እያጎለበቱ ለብዙዎች ተስፋን መፈንጠቃቸውን ቀጥለዋል'' ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለጥፋት መንገደኞች ጀርባውን በመስጠት ዐቅምና ጉልበቱን ለሁለንተናዊ ብልጽግናው እንደሚያደርግም ዶክተር ዓቢይ እምነታቸው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም