በሕንድ የዓለማችን ትልቁ ዕጢ በቀዶ ጥገና ተወገደ

102

ነሐሴ 18/2012(ኢዜአ) በሕንዷ ዋና ከተማ ኒው ዴልሂ በሚገኝ አንድ የግል ሆስፒታል ያሉ ሀኪሞች የዓለማችንን ትልቁ የኦቫሪ ዕጢን ከ52 ዓመት ሴት አካል አስወገደ።

አናዶል የዜና ምንጭ እንደዘገበው፤ ዓምስት ሰዓታት በፈጀው የቀዶ ጥገና የተወገደው እጢ 54 ኪሎግራም ወይም (119 ፓውንድ) የሚመዝንና የሕመምተኛዋ ክብደት ግማሽ ነው ተብሏል።

ባለፉት 30 ዓመታት የሥራ ዘመን የሰውነት ክፍልን ግማሽ የሚመዝን እጢ አጋጥሟቸው እንደሚያውቅ የአፖሎ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ቀዶ ጥገና እስፔሻሊስትና አማካሪው አረን ፕራይድ ተናግረዋል።

የዴልሂ ነዋሪ የሆነችው ህመምተኛዋ ከቅርብ ወራት ወዲህ ህመሙ ክብደቱን እያሳደገ ወደ 106 ኪሎ ግራም (234 ፓውንድ) ደርሶ እንደነበር አስታውሳ፤ በዚህም የተነሳ መተንፈስ ፣ መራመድ እና በሆድዋ ላይ ከባድ ህመም አጋጥሟት እንደነበር ዘገባው አመልክቷል።

ከዕጢው ትልቅነት የተነሣ የቀዶ ጥገና ሂደቱ ወቅቱ ባፈራቸው ቴክኖሎጂ ግብዓቶች ለመጠቀም አስቸጋሪ አድርጎት እንደነበር ያመለከተው ዘገባው፤ በዚህም የቀዶ ጥገናው ቡድን ዕጢውን ለማስወገድ በባህላዊ መንገድ ለመጠቀም መገደዱን አመልክቷል።

ፕሬይድ እንደተናገሩት “በዕጢው ትልቅነት ምክንያት ፣ በህመምተኛዋ የሆድ ዕቃ ክፍሏ ላይ ሁሉ ዕጢው ተጭኖ እና አንዳንድ የአንጀት ክፍሎችም ተበላሽቶ ነበር ።

ይሁን እንጂ እንደ እድል ሆኖ ዕጢው ጤናማ ያልሆነ እና በህመምተኛዋ ላይ ተጨማሪ አደጋ ሊያስከትል የሚችል በሽታ ስላልነበረው ህመምተኛዋ በፍጥነት እንድታገግም አስችሏታል ፡፡

ከቀዶ ጥገናው በኋላ የህመምተኛዋ ክብደት ወደ 56 ኪሎግራም (123 ፓውንድ) መቀነሱንም ዘገባው አመልክቷል ፡፡

ከግለሰቧ የወጣውም ዕጢ በዓለማችን በቀዶ ጥገና የወጣ ትልቁ እጢ እንደሆነም ዘገባው አመልክቷል።

እ.ኤ.አ. በ 2017 በደቡባዊው ኮምቢቶሬ ከተማ በተመሳሳይ ሁኔታ ከታመመች ሴት የ 34 ኪ.ግ (75 ፓውንድ) ዕጢ በቀዶ ጥገና ተወግዶ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም