በከተማ ግብርና የተሠማሩ ዜጎች ምርታቸውን ለገቢያ ለማቅረብ እየሠሩ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በከተማ ግብርና የተሠማሩ ዜጎች ምርታቸውን ለገቢያ ለማቅረብ እየሠሩ ነው
ነሀሴ18/2012(ኢዜአ)በኮቪድ19 ምክንያት ሊፈጠር የሚችለውን የምግብ እጥረት ለመቅረፍ በተሰጣቸው ቦታለገቢያ የሚቀርቡ አትክልቶችን በማልማት ላይ እንደሚገኙ ወጣቶች ገለጹ።መንግሥት ኮቪድ 19 መከሰትን ተከትሎ የአትክልትና ፍራፍሬ አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በከተማው የሚገኙ ባዶ ቦታዎችን በከተማ ግብርና እንዲለሙ ለከተማው ማኅበረሰብ መስጠቱ ይታወሳል።
ይሄን ተከትሎ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በዘርፉ የተሰማሩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የተረከቡትን ቦታ እንዴት እያለሙት ነው ሲል ቅኝትአድርጓል።
ሃና ታደለ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ አራት ሀና፣ሜሮንና ጓደኞቿ በሚል ስያሜ በማኅበር ተደራጅተው ከወረዳው ቦታ በመረከብ በከተማ ግብርና ልማት የተሰማሩ ወጣቶች ሰብሳቢ ናት፤ ሀና እንደምታናገረው በተረከቡተ ቦታ ሽንኩርት፣ ቀይ ስር፣ ቲማቲም፣ ሰላጣ፣ ጎመን፣ ድንችና የመሳሰሉትን የጓሮ አትክልቶች በማልማት ላይ ይገኛሉ።አቡሽ ወልደሰንበትና ወይዘሮ የሺ ፈይሳ በዚሁ ክፍለ ከተማ መሬት ወስደው በከተማ ግብርና የተሰማሩ ማኅብራትን በሰብሳቢነት ይመራሉ።
የተረከቡትን ቦታ የጓሮ አትክልት ዘርተው በማልማት ለገቢያ ለማቅረብ የዘሩትን አትክልት በመንከባከብ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።ክፍለ ከተማው ቦታ ከመስጠት ጀምሮ ዘር በማቅረብ እንዳገዛቸው የሚናገሩት የማኅበራቱ ሰብሳቢዎች፤ የዘሩት የጓሮ አትክልት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም አስረድተዋል።
በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ምርቱን ለገቢያ እንደሚያቀርቡም ተናግረዋል።በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 የሚኖሩና የአሊና ጓደኞቹ የከተማ ግብርና ማኅበር አባላት በከተማ ግብርናው ዘርፍ 40 ሄክታር መሬት ቦታ ወስደው ወደ ልማት ከገቡ ወጣቶች መካከል ይገኙበታል።የማህበሩምክትልሰብሳቢወጣት በጅጋ ኦልጅራ እንደተናገረው፤ ኮሚሽኑ በፈጠረላቸው የከተማ ግብርና የሥራ ዕድል የተለያዩ የጓሮ አትክልቶችን በመትከልና በመዝራት እየተጠቀሙ እንደሚገኙ አስረድቷል።
የአሊና ጓደኞቹ ማኅበር አባላት በተረከቡት ቦታ ያለሙትን የመጀመሪያ ምርት ለኅብረተሰቡ በማቅረብ በተመጣጣኝ ዋጋ መሸጥ መጀመራቸውንም ገልጸው፤ከሽያጩም 25 ሺሕ ብር ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
ማኅበራቱ መንግሥት እስከአሁን እያደረገላቸውያለውን ድጋፍ አድንቀው፤ ሥራቸው በበጋውም እንዲቀጥል የውሃና የዘር አቅርቦት ድጋፉን እንዳያቋርጥባቸው ጠይቀዋል።ከተቋቋመ አንድ ዓምት ያስቆጠረው የአርሶ አደርና የከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በአራት ወራት ውስጥ ለከተማ ግብርና ከተለዩት 768 ሄክታር መሬት ውስጥ 700 ሄክታሩ ሲታረስ፤ 617 ሄክታር በዘር መሸፈኑን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።