የሻደይ፣ አሸንዳ፣ አሸንድዬና ሶለል በአላት በችግኝ ተከላና በሌሎች በጎ ተግባራት ታስበው ሊውሉ ይገባል - ኢዜአ አማርኛ
የሻደይ፣ አሸንዳ፣ አሸንድዬና ሶለል በአላት በችግኝ ተከላና በሌሎች በጎ ተግባራት ታስበው ሊውሉ ይገባል
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 16/2012(ኢዜአ) የዘንድሮውን የሻደይ፣ አሸንዳ፣ አሸንድዬና ሶለል በአላትን ህዝቡ በችግኝ ተከላና በሌሎች በጎ ተግባራት አስቦ ሊውል እንደሚገባ ተገለጸ።
የሻደይ፣ አሸንዳ፣ አሸንድዬና ሶለል "የኢትዮጵያ የልጃገረዶች ጨዋታ" በየዓመቱ ከነሐሴ 16 ጀምሮ እስከ ነሐሴ መጨረሻዎቹ ባሉት ቀናት የሚከበር በአል ሲሆን ይህም በተለይ በትግራይና አማራ ክልል በሚገኙ አካባቢዎች ላይ በስፋት ይከበራል።
ይሁንና በአሉ ዘንድሮ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በአደባባይ ሴቶች ተሰብስበው የሚያከብሩት አይሆንም።
በዚህም በአሉ በስፋት የሚከበርባቸው አካባቢዎች ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ከወረርሽኙ ራሳቸውንና አካባቢያቸውን መጠበቅ ይኖርባቸዋል ተብሏል።
በአሉን በችግኝ ተከላ እና በሌሎችም መሰል በጎ ተግባራት አስበውት ሊውሉ እንደሚገባ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ በአዲስ አበባ የዋግ ህምራ ብሔረሰብ ተወላጆች ገልጸዋል።
በተለይም አገሪቱ አሁን ላይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ የምትገኝ እንደመሆኗ መንግስት ያወጣውን መመሪያ በመከተል እና በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ ራስንና አካባቢን ብሎም አገርን ከወረርሽኙ መጠበቅ ይገባል ብለዋል።
አቶ አስራት ታደሰ በሰጡት አስተያየት የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የጥንቃቄ መንገዶችን በመከተል ህብረተሰቡ በያለበት በጎ ተግባራት ማከናወን ይገባል ብለዋል።
በዋግምራ በተፈጥሮ ሃብት የተጎዱ አካባቢዎች ችግኝ ይተከላል ያሉት አቶ አስራት፤ ሻደይ፣ አሸንዳ፣ አሸንድዬና ሶለል በሚከበርባቸው አካባቢዎች ማህበረሰቡ ራሱን ከቫይረሱ በመከላከል መልካም ተግባራትን በመተግበር ማክበር ይገባል ነው ያሉት።
ወጣት ሜላት ሃይለማርያም በበኩሏ መንግስት ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለዜጎች ጥቅም መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት የጥንቃቄ መመሪያዎቹን በመከተል ችግኝ በመትከልና ሌሎች በጎ ተግባራትን በማከናወን ማክበር እንደሚገባ ገልጻለች።
በዓሉ ፌስቲቫል በመሆኑ በሜዳ ላይና በአዳራሽ በጭፈራና በተለያዩ ጨዋታዎች የሚከበር ቢሆንም በዚህ ወቅት ለኮሮና ቫይረስ ስለሚያጋልጥ ቤተሰብ፣ ልጆችና የአካባቢው ማህበረሰብ በዓሉን ስያከብሩ በቤት ውስጥ በመቆየትና ሌሎች በጎ ተግባራትን በማከናወን ማሳለፍ ይገባል ያሉት ደግሞ ወይዘሮ እመይቱ ጸጋይ ናቸው።
በአዲስ አበባ የሚገኙ የዋግ ልማት ማህበር አባላት በአሉን አስመል