ቀጥታ፡

የኢትዮጵያን አምባሳደሮች በአዲሱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ ስልጠና ሊወስዱ ነው

አዲስ አባበ፤ ነሀሴ 15/2012 (ኢዜአ) በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በአዲሱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ ስልጠና ሊሰጣቸው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም በየትኛውም የዓለም አገራት ኢትዮጵያን ወክለው የሚገኙ አምባሳደሮች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ስልጠና ይሰጣቸዋል ብለዋል።

የስለጠናው ዋነኛ ትኩረትም በአዲሱ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ መሆኑን አምባሳደር ዲና ገልጸዋል።

የስልጠና መርሃ ገበሩም የፊታችን ሰኞ በቢሾፍቱ ከተማ የሚጀመር መሆኑን ተናግረዋል።

በዚሁ አጋጣሚ የኤምባሲዎችና ቆንስላወች ዓመታዊ የስራ አፈፃፅም የሚገመገም መሆኑን ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።ስልጠናው "ዲፕሎማሲያዊ ሰላም ለአገር ብልፅግና" በሚል መሪ ሀሳብ የሚከናወን መሆኑም ተገልጿል።

አምባሳደሮቹ በሸገር፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱና እንጦጦ የተከናወኑ መሰረተ ልማቶችን እንደሚጎበኙም ይጠበቃል።

እንደ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለፃ የዜጋ ዲፕሎማሲ በመካከላቸው ምስራቅ የዜጎች ደህንነት ላይ በስፋት እየተሰራ ነው።

በዚሁ አካባቢ የሚኖሩ 180 ኢትዮጵያዊያንን ሰሞኑን ወደ አገራቸው ለመመለስ የሰነድ ማዘጋጀት ስራ መሰራቱን ጠቅሰው በሌሎች አገሮችም ይሄው ተመሳሳይ ተግባር ይቀጥላል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም