ቀጥታ፡

የዛሬ ዓመት ቃል የገባነውን ፈጽመን በተግባር አሳይተናል--ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ

ነሓሴ 13/2012(ኢዜአ) የዛሬ ዓመት ቃል የገባነውን ፈጽመን በተግባር አሳይተናል ፤አሁን ደግሞ መላው ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በገበታ ለሀገር ተሳትፈው ዐሻራቸውን በኢትዮጵያ እንዲያሳርፉ እንጋብዛለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ10 ሚሊዮንና የ5 ሚሊየን ብር ገቢ ለማድረግ፣ እንዲሁም ከሀገር ውስጥ ማንኛውም መጠን ያለውን የገንዘብ አስተዋጽዖ ለማድረግ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000339911267፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ እንዲሁም ከሀገር ውጪ ሆነው ማንኛውም መጠን ያለውን የገንዘብ አስተዋጽዖ ለማድረግ በባንክ ሂሳብ ቁጥር 0100101300591፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ ማድረግ እንደሚቻል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

በተጨማሪም፣ መላው ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን ያህል የገንዘብ መጠን ለማዋጣት ወደ 333 አጭር የጽሑፍ መልዕክት በመላክ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ጥሪ አቅርበዋል።



የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም